ከቤታችን ጀርባ
ከቤታችን ጀርባ
ክፍል አንድ
✍️ #ፀሀፊ #አቤል #እንግዳ
.... #ከቤታችን_ጀርባ
በህይወት ስንኖር እያንዳንዷ ቀን የሙከራ ጊዜ ናት አለ አንዱ ፈላስፋ ይሄ ንግግር ያለምክንያት ትዝ አላለኝም ሰሞኑን አንድ እንግዳ ነገር ቤታችን ውስጥ በለሊት ሲዘዋወሩ ድምፃቸው ይሰማኛል ግን ምን እና እነማን እንደሆኑ ላውቅ አልቻልኩም ያስፈራል ሽፍንፍን ብዬ ለጥ ማለቴን ቀጠልኩኝ ።
ቤታችን በጣም ትልቅ ቤት ነው ቤተሰቦቼ በፊት ከነበሩበት ሰፈር ለቀን አሁን እኔ በምኖርበት ሰፈር ገቡ የሚገርማችሁ ቤቱን የገዛንበት ብር ወይም የቤቱ ዋጋ በጣም ትንሽ ነው ወደውጭ ልንሄድ ነው ስላሉን ቶሎ ገዝተን ገባንበት ቤተሰቦቼ ሁለቱም በተመሳሳይ ቀን ነው አንድ አይነት አሟሟት የሞቱት በአንድ አይነት ሰአት ቤት ውስጥ ከቤታችን ጀርባ አባ ሁሌ ወደጓሮ እንዳልሄድ ይነግረኝ ነበረ አንድ ቀን አባ ወደ አመሻሹ ላይ ነበረ ወደጓሮ ሲሄድ ብርሀን ነገር ይመለከታል ከመሬት ስር የሚወጣ ብርሀን እናም ፈራ ተባ እያለ ጠጋ ጠጋ ማለቱን ተያያዘው ወደ ብርሀኑ እየተጠጋ ሲመጣ አንደርግራውንድ የተሰራ ቤት አለ ከላይ በጣውላ የተሰራ በር አለው የውጭ ፊልሞች ላይ አንደምናየው አይነት ሁለት ወደ ላይ ተከፋች በሮች አሉት ከፍቶት ለመግባት እየፈራ ወደ ውስጥ አቆልቁሎ እየተመለከተ ደረጃው ያረጀ የድሮ ጣውላ ከጥድ የተሰራ ነው የሸረሪት ድር የደራበት ደረጋ ነው ነገር ግን መሀሉ ብዙ ጊዜ የተሄደበት ይመስላል አፈርም ጭቃም የነካካው ነው የጫማ ኮቴም አለበት አባ ቀስ ብሎ ገባ ገና የመጀመሪያውን መረገጫ ሲረግጠው ሲጢጢጢ አለ ቀስ እያለ ሁለተኛውን አሁንም አንደዛው ሲጢጢ ጥ እያለ አንደምንም 6ቱን የደረጃ እርብራብ ወርዶ ሲጨርስ በጣውላ የተሰራ ወለል ያረጀ የድሮ ፋኖስ የበራበት ቤት ሞቅ ያለ ቤት ነው ግን በጣም የሚያስፈራ ሞት ሞት የሚሸት ቤት ነው ምን ቤት መቃብር አንጂ ሞት ሞት ሞት የሚሸተው መቃብርነው አንጂ ወደ ውስጥ ለመዝለቅ ጠጋ እያለ አሁንም ጠጋ እላዩ ላይ የሚጣበቀውን የሸረሪት ድር እያራገፈ አንድ ሶስት እርምጃ ከተራመደ በኋላ አንዳች ነገር ውርር አድርጎ የያዘው ያክል ተሰማው አንዳች ፍጡር ካረጀው ፋኖስ አጠገብ አጥንት እየጋጠ ወደእሱ አፍጦ ሲያየው አይን ላይን ተፋጥጠው ቀሩ ከኋላው ትካሻው ላይ አንድ ነገር ሲነካካው ተሰማው ደርቆ ቀረ እጅ ነበረ ጠረን ያለው እጅ ለዛውም ሴት ነች ጥፍሮቿ በጣም ከመርዘማቸው የተነሳ ተቆርጠውጨ የሚያቁ ራሱ አይመስሉም ከመቅፅፈት ሀይሌ አንኳን አንደሱ ሮጦ አያቅም
ኡ ኡኡኡኡኡ እያለ በሩጫ ያን ያረጀ የጣውላ መረጋገጫ አንዴት አንደወጣው የቤታችን በር በርግድ አድርጎ አባ ወደውስጥ ገባ ፊቱ ጠቋቁሯል ደሞ አትካሻው በስተቀኝ ወደ ብብቱ አካባቢ ደም ይፈሳል አባ መጮሁን አላቆመም ተዝለፍልፎ ፊታችን ወደቀ እማ ቤቱን በጩሀት አቀለጠችው አረ የሰው ያለህ ኡኡኡኡኡ ብትል አባ ድፍት አለ የሰፈሩ ሰው ግልብጥ ብሎ መጡ ቀድሞ የደረሰው ጎረቤታችን የሆነው ሳጅን አበራ ነበረ ወደወደቀው አባቴ ሲመለከት ደነገጠ ሮጥ ብሎ ከአንገቱ ቀና አደረገው አባ መተንፈስ ጀመረ ግን የሚያወራው አይሰማም ጀ ጀ ጀ ጀ ር ጀ ጀ ብቻ ነው የሚለው ሳጅን ጨነቀው አባ ጣቱን ወደ ውጪ አያመለከተው እስከ ወዲያኛው አሸለበ ቤቱ በለቅሶ ተሞላ ሳጅን ጀ ጀ የምትለዋን የአባዬን ቃል እያብሰለሰለው ነበረ ጠራኝ እስኪ አቡሽ ና አለኝ ሄድኩኝ አባትክ ከመሞቱ በፊት የት ነበረ አለኝ ጓሮ ነበረ አሁን መልስ ያገኘ መሰለው ሮጥ ብሎ አብረውት የነበሩ ሰዎችን አስከትሎ ወደ ጓሮ ሄድን ሰንሄድ ግን ምንም ነገር የለም ባዶ ሳር መሬት ብቻ ሳጅን የሆነ ነገር አንዳለ መጠርጠሩን ቀጠለበት ከዛ ወደ መሀል መጠጋቱን ቀጠለ ወደ መሀል ሲጠጋ አሁንም ምንም ነገር የለም ተስፋ ቆርጠው ሲመለሱ ግን ሳጅን አንድ ነገር አስተዋለ አንድ እግሩን ሲያነሳ ቋ የሚልድምፅ ሰማ ደነገጠ አሁንም ሰማ
ወደ ኋላ አፈገፈጉ ....
"አባትክ ከመሞቱ በፊት የት ነበረ?" አለኝ
" ጓሮ ነበረ " አሁን መልስ ያገኘ መሰለው ሮጥ ብሎ አብረውት የነበሩ ሰዎችን አስከትሎ ወደ ጓሮ ሄድን ሰንሄድ ግን ምንም ነገር የለም ባዶ ሳር መሬት ብቻ ሳጅን የሆነ ነገር አንዳለ መጠርጠሩን ቀጠለበት ከዛ ወደ መሀል መጠጋቱን ቀጠለ ወደ መሀል ሲጠጋ አሁንም ምንም ነገር የለም ተስፋ ቆርጠው ሲመለሱ ግን ሳጅን አንድ ነገር አስተዋለ አንድ እግሩን ሲያነሳ ቋ! የሚልድምፅ ሰማ ደነገጠ አሁንም ሰማ
ወደ ኋላ አፈገፈጉ
ፖሊሱ የደነገጠ ይመስላል ሰዎቹ ተያዩ የሆነ አንዳች ስሜት ወሮ የያዛቸው መሰላቸው ከነሱ መሀል አንደኛው ግን ፊቱ ላይ የላብ ምልክት ይታይበታል በጣም አንደፈራ ያስታውቅበታል
"ተሼ አረ አንደሂድ እኔ ጨንቆኛል " አለ ባትላቸውም እነሱም ጨንቋቸዋል ሳጅን ስልኩን ደውሎ ከአካባቢው ፖሊሶች አንዲመጡ አደረ ዶማ እና አካፋ አንዳመጣ ነገረኝ እና ላመጣ ሄድኩኝ ሀዘኔ ላይ ድንጋጤ ተጨምሮበት ስሜቴን ዘበራረቀው ዶማውንና አካፋውን አመጣውለት አካፋውን ተቀበለኝ እና ለመቆፈር ተዘጋጅቶ አንዴ ሲቆፍር እንዳጋጣሚ ከላይ መጠነኛ አፈር ስለነበረ በአካፋ አፈሩን ከላይ አነሱት (ጠረጉት) ባለሁለት ተከፋች የጣውለ በር ነው ማን ይክፈተው ሌላ ፍርሀት ሳጅን ሽጉጡን አቀባበለ እና
"አንግዲህ ገብተን ማየት ይኖርብናል" ብሎ አብረው ለመጡ የፖሊስ አባላቱ ማሳሰቢያ ሰጠ ። አንዱ ፖሊስን ውጪ ላይ አንዲቆም አደረገው በሩ ሳጅን ከፈተው ውስጡ መጠነኛ የቀን ብርሀን ያለበት ይመስላል ቀስ ብሎ የመጀመሪያውን የጣውላ መረገጫ ተረገጠ ቃ ቃ ቃ አለ ከሀሏ ያሉት ፈራ ተባ እያሉ ተከተሉት ሁሉም ፈርተዋል ወለሉ ላይ ደረሱ ሳጅን አንዲህ አይነት ቤት አይቶ አያቅም ወደ ውስጥ በገቡ ቁጥር የቤቱ ገፅታ ረጅም እድሜ ካመስቆጠሩ የዘለለ ነገር ማስተዋል አልቻሉም ማንም ገብቶበት የሚያቅ አይመስልም ዙሪያውን በደንብ አዩት ምንም ነገር የለም ሳጅን
"በሉ አሁኑኑ አንውጣ ምንም ነገር የለም ዝንብለን ነው የለፋነው " ብሎ ወደ ደረጃው አመራ ሁላችንም ልብ ያላልነው ነገር ከመደርደሪያው ላይ የሻይ ማንቆርቆሪያ ተጥዶ የወረደ አንፋሎቱ በርዶ ያላለቀ ማንቆርቆሪያ አመደርደሪያው ላይ ነበረ የኔ ገልቱነት አንጂ ትንሽ አንፋሎት እኮ አይቼ ነበረ ምን አፌን እደለጎመው ወደ ደረጀው መውጣታችንን ቀጠልን ከእቃ መደርደሪያው ቤት ወደ ደረጃው ወደሚወስደው በስተ ቀኝ በኩል በጣም ጨለም ያለ ቦታ አለ አላስተዋልነውም ወደ ደረጃው ስወጣ የሰው ቅርፅ ያለው ጥላ ሲንቀሳቀስ ያየው መሰለኝ ደንግጬ ይሁን ወይም ስለደነገጥኩኝ አይምሮዬ ላይ ስዬው ይሁን አላውቅም ሁላችንም ወጣን ።
ሳጅን የቤቱን በር ዘጋው በትልቅ ቁልፍም ቆለፈው አፈሩን መልሰው አለበሱት በቃ
"ከዚህ በኋላ ወደዚህ መምጣት አያስፈልግም እሺ " አለኝ ሳጅን እኔም "እሺ" አልኩኝ።
ዛሬ የአባ ሰልስት ነው አዎ ሰዎች እየመጡ እያፅናኑን ይሄዳሉ ወደ 8 ሰአት አካባቢ ግን ጥግ ላይ አካባቢ አግድም መቀመጫው ላይ የሆነ ነገር የተቀመጠ ይመስለኛል ወንበሩ አንጋደደ ሌላ የተቀመጠ ሰው የለም ነገር ግን ከአንድ አቅጣጫ ተንጋዷል ሚዛን ስቷል አፍጥጬ( ትክ ) ብዬ ሳይ ምንም ነገር የለም አሁንም ተንጋዷል ከደቂቃዎች በኋላ ሊያፅናናኝ የመጣን ሰው ተሰናብቼ ፊቴን ዞር ሳደርግ .......
ዛሬ የአባ ሰልስት ነው አዎ ሰዎች እየመጡ እያፅናኑን ይሄዳሉ ወደ 8 ሰአት አካባቢ ግን ጥግ ላይ አካባቢ አግድም መቀመጫው ላይ የሆነ ነገር የተቀመጠ ይመስለኛል ወንበሩ አንጋደደ ሌላ የተቀመጠ ሰው የለም ነገር ግን ከአንድ አቅጣጫ ተንጋዷል ሚዛን ስቷል አፍጥጬ( ትክ ) ብዬ ሳይ ምንም ነገር የለም አሁንም ተንጋዷል ከደቂቃዎች በኋላ ሊያፅናናኝ የመጣን ሰው ተሰናብቼ ፊቴን ዞር ሳደርግ አሁን ወንበሩ ኖርማል ባላንሱን የጠበቀ ሆኗል ይሄ ነገር አይኔ መሆን አለበት የማየት አቅም አነሰ ማለት ነው ገና ሳላረጅ አይኔ ሊከዳኝ ነው አንዴ ።
ታቃላችሁ የምትወዱት ሰው ከአጠገባችሁ ሲለይ በጣም ነው ድብርብር የሚለው አደለም በህይወት አጥታችሁት ይቅርና ለስራ አንኳን ከጠገባችሁ ሲርቅ በቃ ተመሳሳይ ስሜት ነው ለዛውም ይሄኛው ከነጭራሹን ተመልሶ አንደማይመጣ ስታስቡት ደግሞ ያማል ግን ያው የተፈጥሮ ህግ ናትና ከፈጣሪን ቃል አምነን ከመቀበል ውጪ ምን እናመጣለን ።
"ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት" አደል የሚለው ቃሉ የሰው ልጅ የኮንትራት ጊዜውን ሲያጠናቅ ተጨማሪ ደቂቃ አይሰጠውም ወይ ወደፈጣሪው አልያም ወደ ሲኦል ይጓዛል ምድራዊ ስራችን የመሄጃችንን መዳረሻ ይወስነዋል ቀኑ አንደጉድ ይነጉደዋል ሰአት ፣ቀን ፣ ወር ፣አመት ፣ምዕተ አመት፣ክፍለ ዘመን እያለ ይቀጥላል እማ በአባ ሞት ምክንያት ክፉኛ ተጓድታለች በዛ ላይ ልብ ድካም አለባት በቃ ተጫዋች የነበረችው እማ አሁን ፀጥታ ወርሷታል ለይምሰል ትስቅልኛለች ስትስቅ ራሱ ከንፈሮቿ ለጥርሶቿ ራሱ ቦታ አይለቁም ።
እማ በበሀሪዋ በጣም ተግባቢ ፣አዛኝ፣ሰው አክባሪ ፣የተቸገረ ሰው ካየች የማታልፍ፣ሩህሩህ፣ በቃ ምን ልበላት እናቴ ስለሆነች አደለም በቃ የእናት ተምሳሌት ናት በአጭሩ ከእናትም በላይ አባ ሁሌ የሚመክረኝ ምክር አለችው በ አራት ነገሮች አትደራደር ይለኝ ነበረ በአገርክ፣በእናትክ፣በሚስትክ እና በእርስትክ ።
ሁሌ ስለሴት ልጅ ክብር ሳያወራልኝ አያልፍም እማን ሲበዛ ይወዳታል ያከብራታል።
"ሴት ልጅ እናትክ ናት፣ሚስትክ ናት፣ሀገርክ ናት፣እህትክ ናት፣ፍቅረኛክ ናት ሁለነገርክ ናት ክብር ለሚገባው ለሰው ልጅ ክብር ስጥ መልሱን ከሰው አትጠብቅ "ይለኝ ነበረ ።
ከሰፈረ ትንሽ ራቅ ብላ ትንሽ ከፍ ያለች ተራራ የማትባል ጉብታ አለች አንዳንዴ እመጣለው ወደዚች ቦታ ነፋሻማ ቦታ ነች አየሩ በጣም ደስ የሚል ነው ወጣ ብዬ እኮ ይሄን ሰላም የሚሰጥ አለም የሆነ ነፋሻማ አየር በአፍንጫዬ እየማግኩኝ በሀሳብ ጭልጥ ብዬ ሄድኩኝ በመሀል የስልኬ መጥሪያ ከሄድኩበት የሰላም አለም ውስጥ ጎትቶ አወጣኝ ስልኬ ላይ ሴቭ ያልተደረገ ቁጥር ነው አላቀውም አነሳውት
"ጤና ይስልኝ" አለ
" አብሮ ይስጥልን ማንልበል" አልኩኝ በተውሳስ ዘለግ ባለ ድምፅ
" መቅደስን ማግኘት እችላለው ጓደኛዋ ነኝ ከትህምርት ቤት ነው የምደውለው" አለኝ
"ይቅርታ ወንድሜ ተሳስተካል መቅደስ የምትባል ሴት አላውቅም ተሳስተካል ወንድሜ " አልኩት
" እሺ በጣም ይቅርታ " ብሎ ስልኩን ዘጋው ።
ከዛ ጥቂት ደቂቃዎች ከሳለፍኩኝ በኋላ ወደ ቤት ጉዞዬን አቀናው እስከ ቤታችን በጣም ተኝቀራፈፍኩ ከተባለ የ15 ደቂቃ መንገድ ነው ቤት ደረስኩኝ የግቢያችን ድባብ ደባሪ ነው ይጨንቃል በተለይ አባ ካረፈ በኋላ ሂድ ሂድ ሁሉ አይለኝም ቤት ገብቼ ራሱ ለመጋደም ካልሆነ በቀር አስጠልቶኛል ።ዛሬ እኮ አባ የሞተበት ቀን ነው ሰአቱም አንደዛው ወደ ቤታችን በረንዳ ስቃረብ አንድ አንግዳ ነገር አየው የደም ጠብታ ከውጭ ወደ ቤታችን ወደ ሰሎን ሮጬ እማ እማ እያልኩኝ ወደ ውስጥ ስገባ እማ አባ የሞተበት ቦታ ላይ በደም ተለውሳ ወድቃለች።
ጨነቀኝ ምንይሆን ግን ከጀርባችን ያለው ድንኳኑ ሞቋል ካርታ የሚጫወቱም ወጣቶች እንዲሁም ትላልቅ ሰዎችም ጨዋታውን ሞቅ አድርገውታል ሰውም እያሙም ቢሆንም የሰፈሩ ሰዎች እኔ በሀዘን እንዳልጎዳ በደንብ አድርገው እያፅናኑኝ ነው ።
ዛሬ የእማ የሀውልት ምርቃት ነው በጠዋት አባ መተው ቀስቅሰው ይዘውኝ ሄዱ ሀውልቷ ተመረቀ ቤትም አነስተኛ ፀበል ቅመሱ ተደርጎ አለፈ
ባዶ ግቢ እና ባዶ ትራስ ታቅፎ እንደመተኛት የሚያስጠላ ነገር የለም ቀዝቃዛ አየር ነው ቤቱ ሞቅ እንዲል ብዪ እሳት ማያያዝ ጀመርኩ በረንዳችን ላይ ነበረ የማቀጣጥለው ውጪው በጣም ይበርዳል ሳጅን የገዛልኝን በቆሎ ለመጥበስ እና እራት ለመስራት በዛውም እንዲሞቀኝ ብዬ ነው።
እሳቱ እስኪቀጣጠል ብዬ ወደ ጓዳ ገብቼ ሽንኩርት መክተፌን ተያያዝኩት ምንአማራጭ አለኝ የቤተሰቦቼን ማረፍ ከማመን በቀር ሰራተኛ ለመቅጠር አቅሜ አይፈቅድም አይኔ አያሻሸው ገርደፍ ገርደፍ ማድረጌን ተያያዝኩት ድስቱንም አጣጠብኩኝ
"ቆይ ግን ሽንኩርቱ ግን ለወንዶች ብቻ ነው እንዴ የሚያቃጥለው?"
ከራሴ ጋር እያወራው ተፍ ተፍ እያልኩኝ ሳለ
አንዳች አስደንጋጭ ድምፅ ሰማውኝ
"ኳ "የሚል ነበር የሆነ የሰንሰለት ድምፅም አብሮ ተሰምቶኛል በዛላይ የሆነ የአሜሪካ ፊልሞች ላይ እንደማየው ፖሊሶች የወንጀለኞችን ቤት ሰብረው ለመግባት በሩን ብረት ሲመቱት አይነት ድምፅ ነው የሰማውት ቶሎ ብዬ በሩጫ ወደ በሩ አካባቢ ወዳለው ስልካችን ጋር በሩጫ ስሄዴ ከጎኔ አንዳች ግዙፍ ፍጥረት አጠገቤ ቆሟል እንዴት ብዬ በሙሉ አይኔ ልየው እግሩ በፈጣሪ
"ፈጣሪ ሆይ ህልም ነው በለኝ" ብዬ ሳልጨርስ ማጅራቴን አንዳች ነገር እንደወደቀብኝ ታወቀኝ በአፋጢሜ ተደፋው።
"ፈጣሪ ሆይ ህልም ነው በለኝ" ብዬ ሳልጨርስ ማጅራቴን አንዳች ነገር እንደወደቀብኝ ታወቀኝ በአፋጢሜ ተደፋው።
ስልኬ ይጮሀል ይጮሀል ይጮሀል
የሚያነሳው የለም አሁንም ይጮሀል ይጮሀል
ሰአቱ ከምሽቱ ሁለት ሰአት ከሩብ ነው ደዋዩ ሳጅን ነበረ ይደውላል አይነሳም
"ይሄ ልጅ ምን ሆኖ ነው?" ብሎ የስራ ባልደረባውን ጠየቀው
"እኔንጃ!" ብሎ መለሰለት
"ግን በደህና ይመስልካል?" ብሎ ጠየቀው
"በደህናው ቢሆንማ ያነሳልክ ነበረ ደሞም በቤተሰቦቹ ሞት ክፉኛ ተጎድቶ ማንንም ማናገር ባይፈልግስ?" አለው
"አይ በደህናውማ አደለም " ብሎት ይዞት የነበረውን ዶክመንት ወደ ማህደሩ እየመለሰ
"እሲኪ ሄጄ ልየው " ብሎት ወጣ።
በጥድፊያ እየተራመደ ፖሊሳዊ ትርኢት የሚያካሂድ ነው የሚመስለው መንገዷን ቶሎ ቶሎ ላፍ ላፍ አደረጋት
ቤታቸውም አካባቢ ደረሰ ወደ በራቸው ጠጋም ብሎ አንኳኳ
አሁንም ደገመ
ኳኳኳ ኳኳኳ ኳኳኳ
"ሳጅን !" አሉት አንድ መንገደኛ ናቸው
"ሰላም አመሹ!" አላቸው
"እግዚአብሔር ይመስገን እንደምነክ?" እያሉ ጨብጠውት
"በል ደህናእደር" ብለው ተሰናበቱት
"ደህና እደሩ " ብሎ በሩን አንኳኳ አሁንም መልስ የለም
ደግሞ በከባዱ ኳኳኳ
ኳኳኳ ኳኳኳ
መልስ የለም ደነገጠ
"ይሄ ልጅ ምን ሆኖ ነው" እያለ ወደ አጥሮቹ እየተመለከተ ወደ ጎረቤት ግቢ በመሄድ አንኳኳ
ኳኳኳ አደረገ
ከትንሽ ደቂቃ በኋላ በሩ ተከፈተ
"ሳጅን ምነው በሰላም ነው?" ብላ በድንጋጤ እያየችው
"አዎ በሰላም ነው ተረጋጊ" ብሎ ትካሻዋን ቸብ ቸብ እያደረገ
"ይሄ ልጅ እኮ አሳስቦኝ ነው የመጣውት " አላት
"ስልክ አትደውልለትም እንዴ" አለችው
"ደውዬለታለው አያነሳውም በሩም አይከፈትም " አላት
"አንተ ነክ እንዴ ያንኳኳከው?" አለችው
ባለቤቷም ሳጅን ደና አመሸክ ብሎት እሱም ተቀላቀላቸው
ሳጅን አንድ ሀሳብ አመጣ በአጥር ዘሎ ለመግባት እና በሩን ሊከፍትላቸው ወስኖ በጎረቤት አጥር በኩል ዘሎ ገባ።
ባለቤቷም ሳጅን ደና አመሸክ ብሎት እሱም ተቀላቀላቸው
ሳጅን አንድ ሀሳብ አመጣ በአጥር ዘሎ ለመግባት እና በሩን ሊከፍትላቸው ወስኖ በጎረቤት አጥር በኩል ዘሎ ገባ።
ፀጥ ረጭ ብሏል በረንዳው ላይ እሳቱ ፍክት ብሎ የተያያዘ ማንደጃ ተቀምጧል ግራ ገባው
"ይሄ ልጅ የት ሄዶ ነው" ብሎ ጭራሽ ግራ ገባው።
ቀስ ብሎ ወደ ዋናው በር በመሄድ በሩን ከፈተላቸው ገቡ
"በስመአብ በወልድ" ብላ አማተበች
"ምነው " አላት ባሏ
"አሰንዴ ይጨንቃል በፈጣሪ " አለች
"አትንቦቅቦቂ " አላት እሱ ራሱ እየፈራ
"በቃ እንግባ" ብሎ ሳጅን መንቀሳቀስ ሲጀምር
"እንዴ ቆይ በናታችሁ ይቅርብን " አለቻቸው
" አዎ እውነቷን ነው ቢቀርብንስ " አለ ባለቤቷ
" አይሆንም መሳሪያ ይዣለው " ብሎ ሽጉጡን አቀላልቦ ወደ ቤቱ መጠጋት ጀመረ እነሱም ተከተሉት በረንዳው ላይ ያለውን ማንደኛ ጎኑን ነክቶ
" አሁን ነው የተቀጣጠለው ግሏል" ብሏቸው ወደ በሩ ሲጠጋ በሩ አልተዘጋም ነበረ በሽጉጡ ጫፍ ገርበብ አደረገው ሳሎኑ ኦና ሆኗል ይቀዘቅዛል ማንም የለም ወደመኝታ ቤቱ ሄዱ ቀስ ብለው ተጠጉ መብራቱ ጠፍቷል ፈሩ ማን ይድፈር ጨነቃቸው ሳጅን ቁና ቁና እየተነፈሰ የበሩን እጀታ ግጥም አድርጎ ከፈተው እንዴትም ብሎ እጁን ሰዶ መብራቱን አበራው ።
አሁንም የለም ሻወር ቤትም ሄዱ አሁንም የለም
"ምናልባት ጓዳ ሊሆን ይችላል " አለች
ጓዳ በፍጥነት ሄዱ ሲደርሱ ሁሉም አፈጠጡ አይናቸውን አፈጠጡ የተከተፈው ሽንኩርት መሬት ላይ ተዘርግፋል በዛ ላይ ለሀጭ የሚመስል ነገር አለበት ደስቱም በአፍጢሙ ተገልብጧል እንዲሁም ሌሎች እቃዎችም ተገለባብጠዋል ይባስ እየደነገጡ እየተጨነቁ መጡ ሳጅን ፊቱ ላይ ድንጋጤ ይነበብበታል እስኪ ወደ ጋሮ እንፈልገው ብለው ተከታትለው በመውጣት ላይ ሳሉ ከሶፋው ጀርባ በቆሎ ሲኒቀሳቀስ ታያለች
"በፈጣሪ ! " ስትል ይሰሟታል ቁና ቁና እየተነፈሰች አንዳች ነገር የያዛት ይመስል
"ምንድን ነው " አላት ባሏ
"በቆሎው" ብላ ጠቆመቻቸው
ሳጅን ወደ በቆሎው አተኩሮ እያየ አንዴት ሊንቀሳቀስ ቻለ ብሎ በፖሊሳዊ ጥርጣሬ መሳሪያውን ደቅኖ ወደ ሶፋው ጀርባ መጠጋት ጀመሩ የሚያዩትን ማመን አቃታቸው
አቡሽ ነው ድፍት ብሎ
"አቡሽ .... አቡሽ ...... አቡሽ.... አንተ አቡሽ " ቢሉ ቢሉ
አቡሽ ምንም ንቅንቅ አልል አለ።
ሳጅን ወደ በቆሎው አተኩሮ እያየ አንዴት ሊንቀሳቀስ ቻለ ብሎ በፖሊሳዊ ጥርጣሬ መሳሪያውን ደቅኖ ወደ ሶፋው ጀርባ መጠጋት ጀመሩ የሚያዩትን ማመን አቃታቸው
አቡሽ ነው ድፍት ብሎ
"አቡሽ .... አቡሽ ...... አቡሽ.... አንተ አቡሽ " ቢሉ ቢሉ
አቡሽ ምንም ንቅንቅ አልል አለ።
ሳጅን ቶሎ ብሎ የእጄን የልብ ምት ቼክ አደረገ
"ሰዎች! አልሞተም" አላቸው
"እና ምን አንጠብቃለን ወደ ሆስፒታል አንሂዳ አለ " ባለቤቷ የድንጋጤ ፊት አየታየበት
ለሁለት አንዳቸው እጄን አንዳቸው ደሞ እግሬን ይዘውኝ ሲሄዱ የሆነ ነገር ተሰምቶኛል ማን አንደሚወስደኝ ግን አላቅም በቃ በሰመመን መጓዝ ነው ብቻ ከደቂቃዎች በኋላ አንድ ነገር ላይ ሳርፍ ይታወቀኛል ለካ ሆስፒታል ነው እጄ ላይም የሆነ ነገር ሲገባ ይታወቀኛል ለኔ ህመም ባይሰማኝም አይኔንም መግለጥ ቢያቅተኝም ብቻ አንድ ነገር አንደተፈጠረ ይሰማኛል
ዶክተር "ምኖቹ ናችሁ " ሲል ይሰማኛል
"እኔ ሳጅን ተፈሪ እባላለው የአባቱ ጓደኛ ነኝ አንዲሁም ጎረቤቶቹ ነን " አለ ቀልጠፍ ብሎ
"ዶክተር ምን መጥፎ ዜና አለ አንዴ ?" አለው ሳጅን ዶክተሩን
"አረ በጭራሽ በጣም በጥሩ ጤንነት ላይ ነው ጉልኮስ ብቻ ነው የሚያስፈልገው እሱን ሲጨርስ ይሄዳል " አላቸው እሺ ብለውት ወደ አንግዳ ማረፊያው ቁጭ አሉ ።
ከሰአታት በኋላ አይኔን ገለጥኩኝ የሆነ ለብዙ ዘመናት ጨለማ ቤት ውስጥ የተዘጋበት ሰው ነው የመሰልኩት አይኔን ስገልጥ በጣም ነጭ ሆኖ ታየኝ ሳጅን በመንቃቴ ደስ ብሎት ወደ እኔ እየመጣ
"ነቃክ አንዴ ልጄ "እየለ አንዴ የለበስኩትን ልብስ እያስተካከለ አንዴ ደሞ የራስ ምታቴን ቼክ አንደማድረግ እያለ ደህንነቴን ጠየቀኝ ።
እኔም መቼ አንደመጣው እየጠየኩት
"ቆይ ምን ሆነክ ነው አንደዛ ድፍት ያልከው ?" ብሎ ወገቤን የሚሰብር ጥያቄ ጠየቀኝ እኔንጃ አልኩት ለመደበቅ እየጣርኩኝ
"የሆነ ነገርማ አለ የደበከኝ" አለኝ በጥርጣሬ አይኑ እያየኝ
ልጄ ከኔ ትደብቀኛለክ ብዬ አላስብም
"አረ እኔ ልደብቅክ ብዬ አደለም ያለኋኝ ጠያቂ አንተ ብቻ እኮነክ ካንተ ምን እደብቃለው ብለክ ነው ብቻ እኛ ቤት እየሆነ ያለው ነገር ምንም አላማረኝም ብቻ ያስፈራል እኔንጃ ጨንቆኛል "አልኩት
ይገባኛል ወይ ካልሆነ አብሬክ ለአንድ ሳምንት አንተ ጋር መቆየት እችላለው እስክትረጋጋ እሺ ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ አንተ ጋር እመጣለው ።
የሚገርም እኮ ነው የአንተ መውደቅ ሲገርመኝ ድስቶቹ የተደፋበት ቦታ እና አንተ የወደክበት ቦታ ይለያያል
"ድስቶቹ? ነው ያልከው
"አዎ" አለኝ በእርግጠኝነት
"ከምር ! አረ በጭራሽ እኔ ከመመታቴ በፊት ብዬ ንግግሬን ሳልጨርስ "ከመመታቴ ነው ያልከው አለኝ አዎ ተመትቼ እኮ ነው የወደኩት ደሞ የተመታውት ሳሎኑ ውስጥ ነው ።
ማነው የመታክ አለኝ መልኩን አላየሁትም ነገርግን ከወገብ በታች ያለው የሰውነቱ ክፍል ሙሉ ፀጉር በጣም የጠቆረ ሰውነት እግሮቹ የሰው ያልሆነ ግዙፍ ነው ደንግጬ ስለነበረ ከወገብ በታች አይቼ ቀና ልል ስል ነው በምን ራሱ አንደመቱኝ አላቅም አንደመቱኝ ልበል አንጂ አንደመታኝ ከዛ በኋላ አላቅም ምን አንደተፈጠረ ።
ሳጅን ጭራሽ ግራ ገባው የኛ ቤተሰብ ታሪክ ምን ድኖ ነው እዚህ ቤተሰብ ላይ የተፈጠረው እያለ ራሱን በጥያቄ አጣደፈ ።
ግሉኮሴን ጨርሼ ጠዋት 2:45 ሲል ከሆስፒታል ወጣን ሳጅን እኔን ቤት አድርሶ ቤት የተመሰቃቀለውኖ አስተካክለን እሱ ወደስራው ሄደ እውነት ቤታችን እያስጠላኝ መጣ አይመሽ የለ መሸና ወደመኝታዬ ሄድኩኝ ከፀለይኩኝ በኋላ የራስጌ መብራታቸንን አጥፍቼ ትራሴን አቅፌ ለጥ ለካ ደክሞኝ ነበረ አንዴ አንቅልፍ ዥ አድርጎ ወሰደኝ ። ጠዋት ስነሳ እራሴን ሳሎን አገኘውት ከነ ብርድልብሴ ሳሎን ሶፋ ላይ ተኝቼ ደነገጥኩኝ በፈጣሪ ቶሎ ብዬ ወደውጪ ነው በሩጫ የቤታችንን በር ከፍቼ የሄድኩት እንዴ በፈጣሪ እንዴት ሊሆን ቻለ ማታ አልጋ ላይ ነው የተኛውት አንዴት?
ለሳጅን ምንም ሳላስቀር ነገርኩት በጣም ሳቀብኝ አቡሽ በአንቅልፍ ልብክ ሄደክ ይሆናል ብሎ ሳቀብኝ ስቆ የሚያቅ ሁሉ አይመስልም
"አሁን በዚህ ሰአት ይሳቃል አኔ ጨንቆኝ " በፈጣሪ
ዛሬም ማታ አንደዚው ማታ አልጋ ላይ ተኝቼ ጠዋት ስነሳ ሳሎን ሶፋ ላይ ነቃው እኔ ራሱ በህልሜ እየመጣው መሆን አለበት ብዬ ማመን ጀመርኩኝ ።
ዛሬ አርብ ነው ቀኑ አረብ የማልወደው ቀን ነው አይመቸኝም ጭራሽ የሆነ ጨለማ የሚመስል ቀን ነው ለኔ
ያው አንደተለመደው ተመሳሳይ የቀን ውሎዬን አጠናቅቄ ሰአቱን ለምሽት የእለትተዕለት ድርጊቴ ቀጠለ ፀሎቴን አድርሼ ወደ አልጋዬ ዛሬማ የሰሞኑን አዲስ ነገር የማውቅበት ቀን ነው አልተኛም እንደተለመደው ሰአቱ በግምት ወደ 4:30 አካባቢ ይሆናል አንቅልፌም ሊወስደኝ ያዳፋኛል በቃ አንዴ ሽልብ አንዴ ንቅት በቃ ሰመመን ይመስላል ትንሽ ሸለብ አደረገኝ ከደቂቃዎች በኋላ የመኝታ ቤተ በር ተከፈተ ቀስ ብሎ
ሲጢጢጢ...... ሲጢጢጥ..
ብሎ ተከፈተ ይሄ ሁሉ ሲሆን በሰመመን ነው የሚታወቀኝ የሰው የሚመስል ኮቴ ሰማሁኝ መጀመሪያ የአንድ ሰው የሚመስል ነበረ ከትንሽ እርምጃ በኋላ ግን ሌላም ሰው አንዳለ ተረዳሁኝ በቃ የለበስኩትን ብርድልብስ ከገላዬ ላይ ሲጎትቱት ይሰማኛል ምን አንደሆነ አላቅም ለመንቃት እየፈለኩ አልቻልኩም ቀዝቀዝ ያለ እጅ መሳይ ነገር ከወገቤ በኩል እና ከእግሬ በኩል ሲገባ ይታወቀኛል የሚኮሰኩስ ሰውነት ከአልጋዬ ላይ አነሱኝ።
አሁን በዚህ ሰአት ይሳቃል አኔ ጨንቆኝ " በፈጣሪ
ዛሬም ማታ አንደዚው ማታ አልጋ ላይ ተኝቼ ጠዋት ስነሳ ሳሎን ሶፋ ላይ ነቃው እኔ ራሱ በህልሜ እየመጣው መሆን አለበት ብዬ ማመን ጀመርኩኝ ።
ዛሬ አርብ ነው ቀኑ አረብ የማልወደው ቀን ነው አይመቸኝም ጭራሽ የሆነ ጨለማ የሚመስል ቀን ነው ለኔ
ያው አንደተለመደው ተመሳሳይ የቀን ውሎዬን አጠናቅቄ ሰአቱን ለምሽት የእለትተዕለት ድርጊቴ ቀጠለ ፀሎቴን አድርሼ ወደ አልጋዬ ዛሬማ የሰሞኑን አዲስ ነገር የማውቅበት ቀን ነው አልተኛም እንደተለመደው ሰአቱ በግምት ወደ 4:30 አካባቢ ይሆናል አንቅልፌም ሊወስደኝ ያዳፋኛል በቃ አንዴ ሽልብ አንዴ ንቅት በቃ ሰመመን ይመስላል ትንሽ ሸለብ አደረገኝ ከደቂቃዎች በኋላ የመኝታ ቤተ በር ተከፈተ ቀስ ብሎ
ሲጢጢጢ...... ሲጢጢጥ..
ብሎ ተከፈተ ይሄ ሁሉ ሲሆን በሰመመን ነው የሚታወቀኝ የሰው የሚመስል ኮቴ ሰማሁኝ መጀመሪያ የአንድ ሰው የሚመስል ነበረ ከትንሽ እርምጃ በኋላ ግን ሌላም ሰው አንዳለ ተረዳሁኝ በቃ የለበስኩትን ብርድልብስ ከገላዬ ላይ ሲጎትቱት ይሰማኛል ምን አንደሆነ አላቅም ለመንቃት እየፈለኩ አልቻልኩም ቀዝቀዝ ያለ እጅ መሳይ ነገር ከወገቤ በኩል እና ከእግሬ በኩል ሲገባ ይታወቀኛል የሚኮሰኩስ ሰውነት ከአልጋዬ ላይ አነሱኝ።
ከአልጋዬ ወደ ሳሎን ይመስለኛል ይዘውኝ ሲሄዱ የቀኝ እጄ አምልጧቸው ማሬት ላይ ሲያርፍ በጣም አመመኝ ያኔ ነቃውኝ ቀና ብዬ ሳየው ቤታችን ጨለማ ነው ነገር ግን ከውጪ የሚገባው የፓውዛ መብራት ጨረር አልፍ አልፎ ይታያል ሲንቀሳቀሱ አልፎ አልፎ ይታዩኛል ሁለት ናቸው አንደኛው ፂማም ነው በጣም ፂማም ነው አንደኛው ደሞ የተቃጠለ ፊት አይነት ያለው ነው እጃቸው ደሞ በጣም የሚኮሰኩስ ይሰቀጥጣል ።
ወደ ጥግ ሄዱ እና አውረተው መጡ የሚያወሩት ቋንቋ እኛ ከምናወራው የተለየ ነው ልሳን ነው በቃ ጨነቀኝ ወጥተው ሄዱ ወደ ጓሮ እንደሆኑ ያስታውቃል ከጀርባ የተከፈተ የበር ድምፅ ተሰማኝ ።
"በቃ ሳጅን የቆለፈው በር መሆን አለበት " አልኩኝ
ሰውነቴ ተሳስሯል መንቀሳቀስ ሁሉ ከበደኝ ጨነቀኝ በፈጣሪ ምንድነው ግን ያደረጉኝ እኔንጃ ደስ የማይል ነገር እየተሰማኝ ነው ብቻ ፈጣሪ ይጠብቀኝ ብዬ ሳልጨርስ የቅድሙ የበር ድምፅ ተሰማኝ ብዙም ሶይቆይ የሳሎናችን በር ተከፈተ ቀስ ብሎ ሲጠጢጢጢ
ሲጢጢጢ ሲጢጢጥ ብሎ ገርበብ አለ በቃ ሽንቴን ልለቀው ምንም አልቀረኝም በፍርሀት ከዛ ትንሽዬ ህፃን ልጅ የጭንቅላት ቅሉ ጠመም ያለ አይኖቹ ትላልቅ ነጫጭ የአይን ብሌኖች ያሉት በእጁ ትንሽዬ ዱላ ይዟል ዱላው ላይ በሚስማር የተመታ ሽቦ ተጠቅልሎበታል ከዛ እሱን ተከትሎ ሶስት ትላልቅ ትካሻቸው ሰፋፊ የሆኑ የጨረቃ ውዳቂ የማያክሉ ሰዎች ናቸው ምን ሰዎች እላለው ምናቸው የማይታወቅ ፍጡር አንጂ ሁለቱ የተሳለ ቢላ ይዘዋል አንደኛው ደሞ ዘንቢል ወደእኔ መጠጋት ጀመሩ አንዱ ለሀጩ ከአፉ ላይ ወርዶ ፂሙን ተንተርሶ ደረቱ ላይ ከተጣበቀው ብጫቂ ቲሸርት ላይ ፈሰሰ መጠጋታቸውን ቀጠሉ በቃ እንደሞትኩኝ አመንኩ ደሞ ጠረናቸው ሲያስጠላ ቄራ አንኳን አንደዚ አይጠነባም ትንሹ ቀድሞ ነው የተጠጋኝ እናም በእጆቹ እጄን እየዳበሰ የሆነ ሰው አይቶ አያቅም መሰለኝ ፍጥጥ ብሎ ነው የሚያየኝ አሳዘነኝ እኔን ብሎ አዛኝ ቅቤ አንጓች።
በቃ ሞት ሸተተኝ አቅሌን ሳትኩ
"ኡ ኡ ኡኡ ኡ "ብዬ ያለ የሌለኝን አቅሜን ተጠቅሜ ጩሀቴን አቀለጥኩኛ ህሳኑ ደንግጦ ለቅሶ አይሉት ጩሀት አይሉት አቀለጠው ።
"ኡ ኡ ኡኡ ኡ "ብዬ ያለ የሌለኝን አቅሜን ተጠቅሜ ጩሀቴን አቀለጥኩኛ ህሳኑ ደንግጦ ለቅሶ አይሉት ጩሀት አይሉት አቀለጠው ።
ወዲያው ትልቅየው ጭንቅላቱን ይዞ በቃ የሆነ እንደማበድ አደረገው ተያይዘው ወጡ የሰፈሩ ሰው በየት አድርገው እንደገቡ አላቅም
ምንድን ነው ምንድን ነው እያሉ ግማሹ ፍልጥ የሚያካክል ዱላ ግማሹ መኪና የሚያካክል ድንጋይ ይዘው ነው የመጡት በቃ ሳጅንን ሳየው ሮጬ ተጠመጠምኩበት
ምንሆነክ ነው እያለ ግጥም አድርጎ አቀፈኝ ።
እስክረጋጋ ድረስ ዝም አሉኝ ከዛ ሁሉም ቤት ገብተው ተቀመጡ አረጋግተው ጠየቁኝ የተፈጠረውን በሙሉ ምንም ሳላስቀር ነገርኳቸው አላመኑኝም ሳጅን ግራ ገባው እንዳጋጣሚ ሆኖ ክንዴ ላይ ጭረት ነበረ እሱ አሳመናቸው መሰለኝ ሳጅን ምንድነው ይሄ ነገር አንዴ እኔ እኮ ግራ ገባኝ እዚህ ቤት ውስጥ እየተፈጠረ ያለው ነገር አልገባኝም ብሎ ከሌሎች ቤት አብረው ከመጡ ሰዎች ጋር ማውራት ጀመሩ ።
እንዲ አንዲያ እያለ ሌሊቱን ሲያጫውቱኝ ስንጫወት አነጋነው ጠዋት ላይ ሁሉም ከአንቅልፋቸው ተነስተው ወደየ ስራቸው ሄዱ ሳጅንም ልጄ በል ተነስ ና እዚህ መሆንህ ላንተም ጥሩ አደለም አብረኋኝ ስራ ቦታ ትውላለክ ብሎኝ አብረን ሄድን ።
ሳጅን ከሚባለው በላይ ለስራው የሚጠነቀቅ ጥንቁቅ እና ታማኝ የፖሊስ ባለሙያ ነው ለዚህም ማሳያ በቀን በስራው እና በታማኝነቱ ምክንያት የሚመጡ ቡዙ ክሶችን ከነወንጀለኞቹ በማንጠልጠል ለፍርድ በማቅረብ ይታወቃል ።
በቃ ቢሮው መተው የሚያመሰግኑት ሰዎች ብዙ ናቸው አንዲህ አንዲያ እያለ ምሳ ተበላ ጓደኞቹን አስተዋወቀኝ ደስ የሚል ቀን አለፈ እዛው ስራ ተዋለ ከዛም ማታ 12:00 ሲል ከስራ የሚወጣበት ሰአት ነበረ ስራውን ጨራርሶ ወጣን።
ሳጅን "አቤል!" አለኝ
አቤት አልኩኝ ወደቤት መሄድ እየፈለኩኝ
"እስኪ እራት በዚሁ በልተን አንሂድ ዛሬ ካንተ ጋር ነው የምናደርው ጓደኞቼም ይመጣሉ" አለኝ
አኔም ቀበል ብዬ እሺ አልኩኝ እዛው ከመስሪያ ቤት ማለትም ከፖሊስ ጣቢያው ሳይርቅ ገራሚ ምግብ ቤት አለ እዛ ገባን ተውት የምግቡ መአዛ ለጉድ ነው ገና ከውጭ ይጣራል ። አይነት እና ፍርፍር ፣ፓስታ አዘን ማጣጣም ጀመርን ለመጀመሪያ ጊዜ ነበረ ከቤቴ ውጭ ምግብ ስመገብ ከእናቴ ውጪ የሌላ ሰው ምግብ ቀምሼ ስለማላቅ ለመጀመሪያ ጊዜ ከናቴ ውጪ ጣፈጠኝ ።
ወደቤት ገባን ከዛም እነሳጅን አንድ ካሳ ቢራ ይዘው ስለነበረ ዜና እያዩ እኮመኩሙታል ይሄን ቢራ አኔ እንቅልፌ መጣ ሰአቱ ወደ 3 ሰአት ገደማ ይሆናል ።
"ሳጅን ልጄ አንቅልፍህ መጣ አንዴ? " አለኝ አዎን ብዬ መለስኩለት
እሱም "ግባና ተኛ " አለኝ እሺ አልኩኝ
አይዞህ እኛ አለንልክ ተኛ አሉኝ እኔም እነሱን ተማምኜ ገባው ።
ደክሞኝ ስለነበረ ወዲያው ነው እንቅልፍ የወሰደኝ አላውቅም በየት አንደገቡ ባላቅም የሆነ ነገር ሰኒካኝ ይታወቀኛል ሳጅን አጠገቤ ያለ መስሎኝ ዝም ብዬ ወደጎን ተገላበጥኩኝ ይሄኔ ነበረ መልስ ሳጣ ዞር ስል የባለፎው ግዙፉ ፍጥረት ያየውት አቤት የደነገጥኩት አደነጋገጥ በፈጣሪ ቤቱን በጩኋት አቀለጥኩት እነ ሳጅን ከተኙበት ብንን ብለው ተነሱ አቤል አቤል እያሉ ወደ መኝታ ቤት እየሮጡ ሲመጡ ልክ በሩን አንደከፈቱ ገፈታትሯቸው አመለጠ እዛው በወደቁበት ፈዘው ቀሩ አንደኛው ፖሊስ ፊቱ በላቡ ተጠምቋል ተፋጠጡ ምንጉድ ነው እያሉ ይሆናል በሆዳቸው።
ደክሞኝ ስለነበረ ወዲያው ነው እንቅልፍ የወሰደኝ አላውቅም በየት አንደገቡ ባላቅም የሆነ ነገር ሰኒካኝ ይታወቀኛል ሳጅን አጠገቤ ያለ መስሎኝ ዝም ብዬ ወደጎን ተገላበጥኩኝ ይሄኔ ነበረ መልስ ሳጣ ዞር ስል የባለፎው ግዙፉ ፍጥረት ያየውት አቤት የደነገጥኩት አደነጋገጥ በፈጣሪ ቤቱን በጩኋት አቀለጥኩት እነ ሳጅን ከተኙበት ብንን ብለው ተነሱ አቤል አቤል እያሉ ወደ መኝታ ቤት እየሮጡ ሲመጡ ልክ በሩን አንደከፈቱ ገፈታትሯቸው አመለጠ እዛው በወደቁበት ፈዘው ቀሩ አንደኛው ፖሊስ ፊቱ በላቡ ተጠምቋል ተፋጠጡ ምንጉድ ነው እያሉ ይሆናል በሆዳቸው። ሳጅን ከቦታው ተነስቶ ወደ አኔ እየመጣ ልጄ ደህና ነህ አደል አዎን ምንም አልሆንኩም አልኩት ራሴን እየደባበሰ አይዞን ልጄ የገቡበት ገብተን ነው እነዚህን አውሬዎች የማጠፋቸው ዛሬ የመጥፊያቸው ቀን ነው አለኝ እሺ አልኩኝ እሺ ከማለት ውጪ ሌላ መልስ አልነበረኝም ሳጅን አለቃው ጋር ደውሎ አሁኑኑ በፍጥነት የሰው ሀይል ከሙሉ መሳሪያ ጋር ላክልኝ አለው ወድቀው የነበሩት ወገባቸውን እያሻሹ ተነሱ አይዞን ወንድሜ እያለ አረጋጉኝ እውነት ለመናገር በጣም ነው የደነገጥኩት ምክንያቱም ሰው እያለ የመጡ ብቻዬን ካገኙኝ ይገሉኛል ግንጥልጥል አድርገው ነው የሚበሉኝ
ሳጅን የደወለላቸው በፍጥነት ነው የመጡለት ፊልም ነው የመሰለኝ
የጥይት መከላከያ የለበሱ የአዲስ አበባ ፖሊሶች ቦንቦችን የታጠቁ አነፍናፊ የወንጀል ቡድን ውሾች እና ዘመናዊ መሳሪያ የታጠቁ ፖሊሶች ከብረት ለበስ መኪናቸው ተራ በተራ መውረድ ጀመሩ ግቢያችን በፖሊስ አባላት ተጥለቀለቀ ሙሉ ሆነ እነ ሳጅን እና የሳጅን አለቃው ተመካክረው ትዛዝ ሰጡ ሳጅን ወደ ጓሮ እየጠቆመ ከአለቃቸው ትዛዝ መጠባበቅ ጀመሩ ወደ ተዘጋው በር አያመለከቱ በተጠንቀቅ መሳሪያቸውን አቀባብለው እየጠበቁ ነው አዲስ የመጡት የፖሊስ አባላት ፍርሀት እና ምን ይሆን የሚል ስሜት ፊታቸው ላይ ይነበብባቸዋል ።
አለቃቸው ወዲ ወዳ እያየ ይንቆራጠጣል ግርማ ሞገሱ በለው ምን አንደሚያክል ብታዩ ቁመቱ ረዘም ያለ ስልክ አንጨት ብለው አለማጋነን አይሆንብኝም በዚህ ረጅም ቁመቱ ላይ ሰፋ ያለው ደረቱ የግድብ ጫፍ አስመስሎታል አንዲሁም ቦርጩ የጠጅ ብርሌ ይመስላል መልኩም ጨምደድ ያለ ፊት ኮስታራ ፀጉሩም ገባ ገባ ያለ ልክ ትዕዛዝ ሲሰጥ ፊቱ የኮለኔል መንግስቱ ሀይለማሪያምን ፊት ነው የሚመስለው ።
ከደቂቃዎች በኋላ በመነጋገሪያ ሬዲዮናቸው አንድ አጠር ቀጠን ያለ ትዕዛዝ የሰሙ ይመስለኛል ወዲያው ኮስተር ብለው በቆሙበት የፖሊሳዊ ሰላምታ በሬዲዮን ለሰሙት ድምፅ ሰጡ
"እሺ ጌታዬ" የሚል ነበረ
ወደ ፖሊሶቹ እያመራ ሳጅንንም ጠርቶ አሁኑኑ ሽፋን ይሰጥ ኦፕሬሽኑ በ30 ደቂቃ ውስጥ ይለቅ ተብሏ።
ሁሉም የአለቃቸውን ትዛዝ ተቀበሉ ወደ ግዳጅ
የመጀመሪያ 6 ፖሊሶች የድንጋይ መከላከያ መስታወት የያዙ ቀደሙ ከዛም ሳጅን አውቶማቲክ መሳሪያውን እና የጥይት መከላከያውን ለበሰ እና ተከትሏቸው ተጠጋ
ቀስ እድርገው የበሩን ቁልፍ ገነጠሉት ከዛም የጭስ ቦንብ አከታትለው 4 ወደ የተለያየ አቅጣጫ በቤቱ ትይዩ ወረወሩት ወዲያው ገቡ ወደ ውስጥ የመጀመሪያው ወለል ላይ አንደረገጡ የሚንቀሳቀስ ድምፅ ሰምተው ሁሉም ቀጥ አሉ ከፊት የነበረው በእጁ ምልክት ሰጠ ሁለቱ ወደ ግራ አንዲሄዱ 3ቱ ወደ ቀኝ የተቀሩት ደግሞ እዛው ያሉበት ቦታ ላይ ቆሙ።
ድባቡ በጣም የሚጨንቅ ነው ቤቱ ወደ አስፈሪ ስፍራነት ተቀይሯል በስተግራ በኩል የገቡት ሁለቱ ሰዎች ተኩስ ከፈቱ ተኩሱ ከሶስት ጥይት በላይ የተተኮሰበት አይመስልም ወዲያው ቆመ ይመጣሉ ብለው ቢጠብቁ አይመጡም መልስ ይሰጣሉ ቢሉ አሁንም መልስ የለም አለቃቸው ተጨማሪ ሰው እነሱ ወዳሉበት ላከ አንድ ለነሱ ድንጋጤን ምን ድንጋጤ ብቻ ከዛም በላይ መቅሰፍት ነው የተላከባቸው ነው የሚመስለው ከውስጥ ግዙፍ ፀጉሩ በጣም ያደገ ድሬድ የሆነ ፊቱ በጣም እጥፍጥፍ ያለ መስመር ያለበት ጥርሶቹ ደግሞ ግማሹ ያለቀ የተቀሩት የበሰበሱ ቀለማቸውም ከቢጫ ወደ ቀይ ሊቀየር ያለ የለበሰውም ቡትቶ ደረተ ሰፊ የሆነ በእድሜ ቢገመት ወደ 50ዎቹ መጨረሻ የተቃረበ ሲሆን ጉልበቱ ግን በጭራሽ የጎልማሳ አይመስልም ወጣት ሆኖ አንኳን እንደዚ በዛ ላይ የያዘው መጥረቢያ ምን አንደሚያክል ቶር የያዘውን መዶሻ የሚስተካከል ነው በዚህ አንኳን ሰው ተመቶ ድንጋይ ራሱ በሰከንድ ውስጥ ነው የሚሰነጥቀው ።
ወዲያው ነው ተኩስ የጀመሩት የመጀመሪያ ሰውዬ የተኮሰው በስተቀኝ ደረቱ ላይ ነው ያረፈው እንደዛም ሆኖ ሲደግሙት ራሱ ምንም አልመሰለውም ጭራሽ ፊትለፊት የነበረውን በክንዱ ብሎ ግድግዳ ስር ከተተው ቢተኩሱ ወይ ፍንክች ምነም ነገር አልሆነም በዚህ የተናደደው አንደኛው የፖሊስ አባል ጭንቅላቱ ላይ አነጣጥሮ መትቶ ጣለው መሬት ላይ ዝርር ሲል ራሱ ልክ መሬቱን እንደነካ ቤቱ ተነቃነቀ በጣም ክብደት ነበረው ።
በቃ ፖሊሶቹ ስራቸውን ያጠናቀቁ ያክል ነው የተሰማቸው መጀመሪያ ወደተገደሉት የፖሊስ አባላት እያመሩ ሲገቡ መጀመሪያ እንደገቡ የሞቱትን ጓደኞቻቸውን ሬሳ ወደ ውጭ ለማውጣት ሳሉ የህፃን ድምፅ ሰሙ ድምፁ ወዳለበት አቅጣጫ ሲያመሩ ፀጉሩ በአፈር የተጨመላለቀ የሚመስል ፊቱ እንደቅድሙ ሰውዬ የሚጨንቅ ጥርሶቹም ቢሆኑ እንደዛው አንደኛው ፖሊስ አሳዝኖት ሲተወው ጓደኛው በድርጊቱ ተበሳጭቶ እንዴት ገዳያችንን ትምራለክ ብሎ ህፃኑን ደፋው አለቃው በድርጊቱ ተናደደ ወዲያው በጣም በድርጊታቸው የተናደደው የህፃኑ ወንድም እና እናቱ ከተደበቁበት በንዴት ወንድምዬው ፍልጥ በሽቦ እና በሚስማር የተጠቀለለ እናትየዋ ደሞ ቢላዋ ይዘው ወደነሱ በዕልህ እየሮጡ ሲመጡ ፖሊሶቹ ያለ የሌለ ሀይላቸውን ተጠቅመው መሳሪያቸው እስኪያልቅ ድረስ የጥይት ናዳ ረፈረፉባቸው ቡዙም ሳይቆይ እራሳቸውን መከላከል ስላልቻሉ እናም አቅም ስለሌላቸው ህይወታቸውን ማዳን አልቻልም አረፉ ሙሉ የቤተሰቡ አባላት አለቁ ሳጅን ለቀሪ አባላቶቹ ሙሉ ቤቱን እንዲፈትሹ አደረገ ማንም እንዳልቀረ አሳወቁት ወዲያው የፎረንሲክ ባለሞያዎች ተጠሩ ሞያዊ ስራቸውን ሰርተው እንደጨረሱ ቤቱ ፈርሶ በአፈር እንዲሞላ ከአለቃው ትዛዝ ተሰጠ።
እኔም የቤተሰቦቼን ነፍሰገዳዮች መጨረሻ ስላየሁም ደስብሎኛል በቃ ከዚህ በኋላ ያለ ፍራቻ እና ያለመሳቀቅ መተኛት መቻሌንም ሳስብ ደስ አለኝ።
ተጠናቀቀ።
Comments
Post a Comment