ሰሞነኛ የከተማችን የመኪና ታርጋ ስርቆት.
ሰሞነኛ የከተማችን የመኪና ታርጋ ስርቆት....
ይሄ የአንድ ጓደኛዬ መኪና ነው... ሰውየው ሀገር ሰላም ብሎ ሳር ቤት መቻሬ ሜዳ አከባቢ መኪናውን ለ30-40 ደቂቃ አቁሞ ሳይት ቪዚት ገብቶ ሲወጣ የፊትና የኋላ ታርጋ ተፈትቶ ተወስዷል....
እንግዲ ይሄ የተለመደው የስፖኪዮ ፣ የስኮርት ጎማ ወይም መኪና ከነነብሱ የመስረቅ ወንጀል አይደለም የፊትና የኋላ ታርጋ ሌብነት እንጂ...
ባለመኪናው ታርጋው መሰረቁን ወዲያው ለፖሊስ ያመለከተና መኪናውንም ከቆመበት በመኪና መጫኛ አስጭኖ ቤቱ ያስገባ ሲሆን... ሌቦቹ ታርጋውን ለምን ምክንያት እንደሰረቁት እና ምን ወንጀል ሊፈፅሙበት እንደሚችሉ ማወቅ አይቻልም...
ግን ለሌሎቻችንም ጥንቃቄ እንድናደርግና በአጋጣሚ ሌላ መኪና ላይ ይሄ ኮድ 2-B09472 AA ታርጋ ለጥፎ ካያችሁት መኪናው ህገ ወጥ ስለሆነ እንድትጠቁሙን ወይም ባካባቢያችሁ ላለ የህግ አካል እንድታሳውቁለት በአክብሮት ይጠይቃችኋል....
Comments
Post a Comment